ልቅረብ ወደፊትህ ትቼ ሁሉን ነገር ቀኖቼም ይለፉ ሳወራ ከአንተ ጋር ማዶ አሻግሬ የሚያባክነኝን ከእግሮችህ ስር ልዎል እያደመጥኩ አንተን አምላኬ በእረፍት ውስጥ አንተን አውቅሀለሁ ክብርህንም እያየሁ ህግህን እማራለሁ በእግሮችህ ስር መሆንን እወዳለሁ ቃልህን እየሰማሁ ዘወትር አፈራለሁ ካንተ ወደ ማን እሄዳለሁ በእግርህ ስር መሆን ማትረፍ ነው አንት እኮ የህይወት ቃል አለህ ነፍሴ ተማርካለች በህግህ ግዜ ልስጥህ እንጂ ሌላ ምን ዋና አለኝ ቃልህንም ገልጠህ የልብህን ንገረኝ ጠልቄ እንዳውቅህ ቀርቤ እንዳመልክህ ስርአትህን አስተምረኝ አደራረግህን አምላኬ በክብርህ ውስጥ በፊትህ መሆን እንዴት መታደል ነው ሰው ከአንተ ውጭ ለማይሞላ ነገር በከንቱ ነው ሚደክመው የህይወቴ ጨለማ ሁሉ ሊበራ የቻለው በምንም ክቶ የማልለውጠው እግዚአብሔር ቃልህ ነው በእግሮችህ ስር ሆኜ በእውነት እራሴን አቀርባለሁ በማይለወጠው ቃልህ ውበትህን እያየሁ በዙፋን ስር ሆኜ በመንፈስ ነፍሴን አፈሳለሁ በማይለወጠው ቃልህ ማንነትህን እያየሁ