ከፍጥረታት በፊት ኢየሱሰ ነበረ አለምም በሙሉ በእርሱ ተፈጠረ የነበረ ያለ በክብር የሚኖር አምላክ ነው እራሱ ያለ እንደ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ደስታ ነው ውድ አንድ ልጁ ወደ አብ መድረሻ ብቸኛ መንገዱ የህይወት ውሀ ነው የሚፈስ ዘላለም ከእርሱ የሚጠጣ ዳግም አይጠማም እነሆ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ የአለምን ሁሉ ሀጥያት በደሙ ሊያሰወግድ የባርያን መልክ ይዞ ሰውን ሆኖ መጣ በእርሱ ላይ አረፈ የሀጥያታችን ቁጣ ክብር ይሁን ለኢየሱስ ክብር ይሁን ለአዳነን መንግስት እና ካህናት ለእግዚአብሔር ልጅ ላደረገን የመማጸኛ ግንብ ማምለጫ መዳኛ አሳልፎ የማይሰጥ እውነተኛ እረኛ ሊቀ ካህናት ነው ኢየሱስ የሚኖር ዘላለም ከእርሱ ደም የሚያልፍ የሀጥያት ጉልበት የለም እነሆ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ የአለምን ሁሉ ሀጥያት በደሙ ሊያሰወግድ የባርያን መልክ ይዞ ሰውን ሆኖ መጣ በእርሱ ላይ አረፈ የሀጥያታችን ቁጣ ክብር ይሁን ለኢየሱስ ክብር ይሁን ለአዳነን መንግስት እና ካህናት ለእግዚአብሔር ልጆ ላደረገን ላለውና ለነበረው በክብርም ለሚኖረው ከሙታንም በኩር ሆኖ ሞትን ድል አድርጎ ለተነሳው ለነገስታት ሁሉ ገዥ ሁሉን ቻይ አምላክ ለሆነው ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ ነው ክብር ይሁን ለኢየሱስ ክብር ይሁን ለአዳነን መንግስት እና ካህናት ለእግዚአብሔር ልጆ ላደረገን አአሜን!