Song Lyrics

አመልክሃለው

Dawit Getachew
Amnihalehu
አንተ ከቶ የማታውቀው በሂወቴ ምን አለ ገና ሳልነግርህ ይገባህ የለ የልቤ እንዳለ ስለዚህ ጥያቄዬን ገትቼ ላምልክህ ላክብርህ ነውና የዘውትር ስራዬ መቀደስ ስምህን እንዲህ እንዲያ እያልኩ ጊዜዬን አልፈጅም አንተን ከፍ ሳደርግ ያንስብኛል ሁሉም የመኖሬ አላማ ለአንተ ክብር ነው ዘላለም ማምለኬን ሁኔታ አይቀይረው ጌታ ከቶ የማታውቀው በሂወቴ ምን አለ ገና ሳልነግርህ ይገባህ የለ የልቤ እንዳለ ስለዚህ ጥያቄዬን ገትቼ ላምልክህ ላክብርህ ነውና የዘውትር ስራዬ መወደስ ስምህን አንተ እኮ ትልቅ ነህ ከነገሮች በላይ ከአፍህ በወጣው ቃል ፍጥረት ፀንቶ የለም ወይ ሁኔታ ያልቃኘው አምልኮና ክብር እሰዋለው ዘውትር ላንተ ለእግዚአብሔር እጆቼን ከፍ አድርጌ ስምህን እባርካለው የሚገባህን ሁሉ ይዤ በፊትህ እቀርባለው በእውነትና በመንፈስ ነፍሴን በፊትህ ላፍስስ ደስ ያሰኝህ መስዋቴ ይሄ ነው የልብ መሻቴ እግዚአብሔርነትህን አመልካለሁ ክብርህን እያየሁ አመልካለሁ ከሁኔታ በላይ አመልካለሁ ፊትህን እያየሁ አመልካለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection