ሁሉን የምትችል የአብርሃም አምላክ ስለ ተስፋ ቃልህ ቅዱስ ስምህ ይባረክ በእምነት በመጽናት ክብርህን ሰጥሃለው አልጠራጠርም ቃልህን አምናለው አዝ፦ እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው ከማየው በላይ ቃልህን አምናለው በምንም አይነት እንደማተወኝ የከፈልክብኝ ኢየሱስ አሳየኝ እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው ከራሴ በላይ ቃልህን አምናለው በዙፋንህ ላይ እንደምትኖር ፀንትህ ለሚወዱህም ዋጋን እየሰጠህ ከጠየኩህ እና ከማስበው በላይ ማድረግ ለሚቻልህ ያለ አንዳች ከልካይ ተስፋን በሚያስቆርጥ ባለቀ ነገር ላይ ህይወት የምትዘራ አንተ አደለህም ወይ አዝ፦ እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው ከማየው በላይ ቃልህን አምናለው በምንም አይነት እንደማተወኝ የከፈልክብኝ ኢየሱስ አሳየኝ እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው ከራሴ በላይ ቃልህን ይዣለው በዙፋንህ ላይ እንደምትኖር ፀንትህ ለሚወዱህም ዋጋን እየሰጠህ በእምነት ጠብቃለው ቃልህን በተስፋ የሚታይ ደመና ለጊዜው ቢጠፋ ሃይሌ አንተ ነህና ፍጹም አልታክትም በአንተ የታመኑትን ከቶ አትጥላችሀውም ክንድህን ታምኜ ባንተ እመካለው የነገርከኝን ተስፋ አደርጋለው በቃልህ ታማኝ አምላክ ነህና እጠብቅሃለው ሆኜ በምስጋና (፫X)