Song Lyrics

አንተ መልካም ነህ

Dawit Getachew
Amnihalehu
ለአፍታ እልፍ ብዬ አሰብኩ የኋላዬን አቤት ቸርነትህ ከስንቱ ታደገኝ ስወጣና ስወርድ ስወድቅ ስነሳ ስንት ምህረት አየሁ ከቶ ማይረሳ የአንተ መልካምነት ዙሪያዬን ከቦታል እንደ አንተ ሚወደኝ ከወዴት ይገኛል ምህረት ቸርነትህን ነፍሴ እያሰበች በቀንም በማታ ትባርክሀለች በሕይወቴ ያለፉ የማልዘነጋቸው ብዙ ው ለታ አለብኝ ቆጥሬ ማልዘልቀው እንባዬን አብሰህ በደስታ ቀየርከው ከቁስልም አልፈህ ጠባሳዬን ሻርከው የአንተ መልካምነት ዙሪያዬን ከቦታል እንደ አንተ ሚወደኝ ከወዴት ይገኛል ምህረት ቸርነትህን ነፍሴ እያሰበች በቀንም በማታ ትባርክሀለች ቀናቶች ነበሩ ወዴት ነህ ያስባሉ (ወዴት ነህ ያስባሉ) ትናንትን ረስቼ እንዴት እንዳስመለጥከኝ (እንዴት እንዳስመለጥከኝ) ግን ቆም ብዬ ሀሳብህን ሳስተውለው እግዚአብሔር ለኔ ያለህ በጎና መልካም ብቻ ነው አንተ መልካም ነህ አንተ መልካም መልካም ብቻ ነህ ለዘላለም (መልካም ነህ መልካም ነህ) እግዚአብሔር (መልካም ነህ) (መልካም ነህ) ቢገባኝም (መልካም ነህ) ባይገባኝም (መልካም ነህ) መልካም ብቻ ነህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection