Song Lyrics

በቂ ነህ

Dawit Getachew
Amnihalehu
ምን ቀረኝ ከእንግዲህ ሁሉን ሰጠኸኝ የመንግሥትህ ወራሽ በልጅህ ሆንኩኝ ከአንተ የተነሳ ተስፋዬ ሙሉ ነው በሚያስጨንቅ ዘመን ቆሜ ስቃለው አንተን እንጂ ሁኔታን ከቶ አላይም በእምነት እንጂ በሚታየው አልሄድም እረፍትና ሰላም የመንፈስም ደስታ ፍለጋ አትሄድም ነፍሴ ከአንተ ወጥታ ዝማሬዬ ነህ የልቤ ደስታ ነፍሴ ረክታለች ውዷን አግኝታ ከበቂም በላይ በአንተ አርፌያለሁ እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው በአንተ ሁልጊዜ ደስ ደስ ይለኛል በአብሮነትህ ልቤ ይጓደዳል እጅህ በሰራት በዚች ቀን ላይ ቆሜ አመሰግናለሁ ስለ ሰላሜ ሀብት ቢሞላ ቢትረፈረፍ ከንቱ ነው ሰላምን ከምንጩ ጨልፎ አያመጣው በሁሉ ሁልጊዜ ደስ የሚያሰኘኝ የአንተ ሰላም ነው በክርስቶስ ያለኝ ዝማሬዬ ነህ የልቤ ደስታ ነፍሴ ረክታለች ውዷን አግኝታ ከበቂም በላይ በአንተ አርፌያለሁ እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው የማያቋርጥ እረፍት የማይነጥፍ ደስታ በማዕበል ውስጥ እረፍት በመናወጥ ፈንታ ከጸጋህ የተነሳ ዝም ብዬ እስቃለሁ ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ተምሬያለሁ የማያቋርጥ እረፍት የማይነጥፍ ደስታ በማዕበል ውስጥ እረፍት በመናወጥ ፈንታ ከጸጋህ የተነሳ ዝም ብዬ እስቃለሁ ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ተምሬያለሁ የማያቋርጥ እረፍት (የማይነጥፍ ደስታ) በማዕበል ውስጥ እረፍት በመናወጥ ፈንታ ከጸጋህ የተነሳ ዝም ብዬ እስቃለሁ ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ተምሬያለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection