Song Lyrics

ፍቅር

Dawit Getachew
Amnihalehu
የእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር በምንስ ይገለፃል አንድያ ልጁን ለሞት እስኪሰጠው ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዷል ፍቅር እጅግ ግድ ብሎት ስለ ሀጢያተኛው ሞት በደላችንን ሁሉ በልጁ ላይ አኖረ አምነን እንድንድንበት ለጻድቅ ሰው የሚሞት በጭንቅ ይገኝ ይሆናል ስለ ሀጢያተኛው ታዲያ ማንስ ግድ ይለዋል እግዚአብሔር ግን ይወደዋል ብዙ አስከፍሎታል የታላቅ ፍቅሩ ጥልቀት ሀጢያት አረገው ልጁን ሀጢያት ማያውቀውን እኛ የሱ ጽድቅ እንድንሆን በምድር ሁሉ ላይ ጻድቅ ስለታጣ የእግዚአብሔር ፀጋ ወደ ምድር መጣ ወንድ ሴት አላለ ድሃ ወይም ሀብታም በኢየሱስ ለሚያምን ኩነኔ የለበትም ብርሃን በራ በጨለማ የነፃነት ጩኸት ተሰማ በሞት ጥላ ለነበሩ ተከፈተ የምህረት በሩ ብርሃን በራ በጨለማ የነፃነት ጩኸት ተሰማ በሞት ጥላ ለነበሩ ተከፈተ የምህረት በሩ (ፍቅር ነው ፍቅር እግዚአብሔር) (ፍቅር ነው ፍቅር እግዚአብሔር)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection