Song Lyrics

አፀደቀን

Dawit Getachew
Amnihalehu
ክብር ምስጋና ይሁን ለ እግዚአብሔር ወዶናልና ከቶ ላይተወን በዘላለም ፍቅር ክብር ምስጋና ይሁን ለ እግዚአብሔር በእራሱ ምሏል ከቶ ላይተወን ታላቅ እርስት ሆነን ወድቀን ሳለን ተጥለን ፡ስንጨነቅ ሚረዳን አተን በደም ተለዉሰን ሳለን በብዙ ስቃይ ተስፋ ቆርጠን አይቶ እጅግ እራራልን ቁስላችንን አጥቦ ፈወሰን ልጁን በወደደበት ፍቅር እኛንም እንዲሁ ወደደን አዝ፦ አዳነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑም ጠራን የእርሱን ፍቅር በጎነት እንድንናገር ተመረጥን ታላቅ ህዝብ አደረገን የተለየን የንጉስ ካህን ምህረትን አግኝተን ተባልን የ እግዚአብሔር ወገን ወገን /3/ ወገን : አደረገን ልጆች /3/ ልጆቹ : አረገን አፀደቀን አምላክ ተብሎ ሊጠራብን እግዚአብሔር ስላላፈረብን ከእርሱ ጋር አብረን እንድንኖር በሰማይ ስፍራ አዘጋጀልን ወደደን ደግሞም አፀደቀን ከእንግዲ ማነው ሚኮንነን ሰቶናል የልጅነት መንፈስ እንድንጠራው አብ አባት ብለን አዝ፦ አዳነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑም ጠራን የእርሱን ፍቅር በጎነት እንድንናገር ተመረጥን ታላቅ ህዝብ አደረገን የተለየን የንጉስ ካህን ምህረትን አግኝተን ተባልን የ እግዚአብሔር ወገን ወገን /3/ ወገን : አደረገን ልጆች /3/ ልጆቹ : አረገን አፀደቀን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection