ደማቁ ብርሃን ባንተ ይሰወራል ህያው ማንነትህ ከዘላለም ያልፋል አቤት ያንተ ውበት ሞገስህ ሲያበራ አትወዳደርም ከሰራኸው ጋራ አዝ: ትልቅ ነህ ከምንልህ በላይ ከገባኸን በላይ፣ ከሰበክንህ በላይ ኃያል ነህ፣ ብለን ካልንህ በላይ ከዘመርንህ በላይ እግዚአብሔር ሆይ ለግዛትህ ወሰን ፍጻሜ የለውም በእጅህ ላይ ናቸው ዛሬ እና ዘላለም ከጊዜ ውጪ የለህ በጊዜ የምትሰራ ዙፋንህ የጸና የለህ የሚያስፈራ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያለህ እና የነበርክ ለዘለዓለምም የምትርኖር በግርማ ሰማይ እና ምድር በክብርህ ተሞልቷል እግዚአብሔኤር አንተን ከቶ ማን ይመስልሃል አንተ ልዩ ነህ /2/ ልዩ ነህ፣ አንተ ልዩ ነህ