Song Lyrics

ኦ ነፍሴ

Dawit Getachew
Amnihalehu
ነፍሴ ሆይ አስቢ ያደረገልሽን እግዚአብሔር ከጥፋት ከልሎ እዚህ ያደረሰሽን ሆኖሽ ቅጥር ከደዌሽ በሙሉ የፈወሰሽ በጭንቅ ሰዓት የደረሰልሽ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ጉልበት የሚያድሰው ምኞትሽን ከበጎ ነገር የሚያረካ እግዚአብሔር ነው ህይወትሽን ያዳነ ከጥፋት መንገድ ከፊት ለፊትሽ ቀድሞ የሚሄድ የውስጥ ሰውነቴ ቅዱስ ሰሙን በቀንም በማታ አክብሩት እርሱን እግዚአብሔር መሃሪ ይቅር ባይ ነውና ነፍሴ ሆይ እያሰብሽ አቅርቢ ምስጋና ኦ ነፍሴ እባክሽ ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው ኦ ነፍሴ እባክሽ ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው ለቁጣው የዘገየ ፍቅሩም የበዛ አምላክ ነውና ለሚፈሩት ሁሉ የምህረት አምላክ ነው የእንደገና ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ መጠን ከአንቺ አስወገደው የሚያስጨንቅሽን እንደ ሚራራ አባት ለውድ ልጆቹ ዘወትር የያዘሽ በሰፊው እጆቹ ነፍሴ ሆይ አስቢ ታላቅ ውለታውን ሁልጊዜ አፍልቂ ለርሱ የሚገባውን ኦ ነፍሴ እባክሽ ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው ኦ ነፍሴ እባክሽ ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው በበረሀው ምድር ምንም በሌለበት ለጥምሽ እርካታ ለድካምሽ እረፍት ከጠላት ፍላጻ ከቀስተኛም ትኩረት ከለላ የሆነልሽ ካንቺ ፍቅር ይዞት በለመለመው መስክ ዘውትር እየመራሽ በጠላትሽም ፊት በዘይት የቀባሽ እንደ በደልሽ ያልከፈለሽ ምህረቱን ያበዛልሽ እግዚአብሔር ነው እንደ በደልሽ ያልከፈለሽ ቸርነቱን ያበዛልሽ እግዚአብሔር ነው ኦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ ኦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection