Song Lyrics

አንተ ብቻ

Dawit Getachew
Amnihalehu
ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ ለክብርህ አህዛብ ቢሰለፍ አይበዛብህም ቢዘመርልህ አያንስብህም ባንሰዋልህ አንተ ያው እግዚአብሔር ነህ የሚመስልህ የሌለህ ለዘላለምም ጸንተሀል ካንተ በላይስ ክብር የታል አንተ ብቻ እግዚአብሔር በዙፋንህ ጸንተህ የምትኖር ታላቅ አምላክ ነህና ክንድህ የጸና ሁሉን በቃልህ ፈጠርክ በእስትንፋስህ ምድርን ሞላህ የሚመስልህ የሌለህ ድንቅ አምላክ ነህ ሐያላን የታሉ አንተ ላይ የተማማሉ ተረት ሆነ ታሪካቸው እስትንፋስህ በተናቸው አንተ ግን በክብርህ እስካሁን እንዳማረብህ ታላቅ ክንድህም አልደከመም ታምር ይስራል ለዘለዓለም አንተ ብቻ እግዚአብሔር በዙፋንህ ጸንተህ የምትኖር ሀያል አምላክ ነህና ክንድህ የጸና ሁሉን በቃልህ ፈጠርክ በእስትንፋስህ ምድርን ሞላህ የሚመስልህ የሌለህ ድንቅ አምላክ ነህ ከፍጥረት ጋራ አብሬ አቀርባለሁ ዝማሬ ባይመጥንህም እንኳን ታላቅ ክብር ዝም ከማለት ይልቅ መጥቻለው ላደንቅህ ታላቅነትህን እያየሁ ዘምራለሁ ሀያል ነህ ሀያል 2 x እግዚአብሔር ሀያል ነህ ክንድህ ሀያል ነው ሀያል ነህ ሀያል 2 x በቻህን ሀያል ብርቱ ነህ ብርቱ 2 x እግዚአብሔር ብርቱ ነህ ብርቱ ነህ ብርቱ 4x ሕያው ነህ ሕያው 2 x እግዚአብሔር ሕያው ነህ ሕያው ነህ ሕያው 2 x ያለህ የነበርክ ሕያው ደግሞም የምትነግስ ንጉስ ንጉስ ነህ ንጉስ ነህ 3 x
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection