Song Lyrics

ይመጣል

Dawit Getachew
Amnihalehu
እንዴት እንሆን ይሆን ፊትለፊት ስናየው ያዘጋጀነውን ጥያቄ ትተነው ፈዘን በውበቱ በሚያስደንቅ ግርማው አይን አይኑን እያየን እሱን ማወደስ ነው ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር ሊወስደን እንድንኖር ከእርሱ ጋር ተስፋችን ኢየሱስ በሀይል ይገለጣል የወጉትም ደግሞ በአይናቸው ያዩታል የእርሱ የሆኑትን ግን ሊወስድ ይመጣል ማደሪያው ከእኛ ጋር ነው እግዚአብሔር እራሱ ህመም ወይም ሀዘን በዛ አይሠማም እንባችንን በሙሉ ታብሶ ከአይናችን ከኢየሱስ ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለን ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር ሊወስደን እንድንኖር ከእርሱ ጋር ተስፋችን ኢየሱስ በሀይል ይገለጣል የወጉትም ደግሞ በአይናቸው ያዩታል የእርሱ የሆኑትን ግን ሊወስድ ይመጣል አዲሷ ኢየሩሳሌም ውበቷ የከተማው የእግዚአብሔር ክብር እና በጉ ብርሀኗ ነው ፀሀይ ወይም ጨረቃ ከቶ አያስፈልግም የአምላኬ መገኘት ያበራዋል ሁሉንም እንሄዳለን በክብር ልንኖር ከእርሱ ጋር ይመጣል በክብር ልንኖር ከእርሱ ጋር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection