Song Lyrics

አቤት ፍቅርህ

Dawit Getachew
Amnihalehu
አቤት ፍቅርህ የሀጥያተኞች ወዳጅ ጓደኛ የጠፋውን ምትፈልግ እረኛ የደሀ አደጎች ሁሉ አባት የምታኖራቸው ባማረ ቤት የመበለቲት ዋና ተሟጋች ጠበቃ ነህ ለተጎዳች ለተጨነቁ ሁሉ ደራሽ የታመሙትን ደግሞ ፈዋሽ አቤት ፍቅርህ ስንቱን ታደገ ከጠፋንበት እየፈለገ ቀና አደረገን ከሸክማችን ጸጋህ ባይረዳን ጠፍተን ነበርን ተማርኬ በፍቅር አመልክሀለሁ ወድቄ ፊትህ በፈቃዴ ደስ እያለኝ ጌታ ኢየሱስ እወድሀለሁኝ ቀኑ ሲመሽ ሰው ሁሉ ሲሄድ የማትቸኩል ለቁጣ ለፍርድ የውስጥ የልብን ሁሉ ተረድተህ እንባን ከአይን ታብሳለህ አሮጌውን ልብስ አውልቀህ ጥለህ የጸጋ ካባን ለእኛ ደርበህ እዳችንንም በመስቀል ከፍለህ ያጸደከን እንዲሁ በፀጋህ አቤት ፍቅርህ ስንቱን ታደገ ከጠፋንበት እያሳደደ ቀና አደረገን ከሸክማችን ጸጋህ ባይረዳን ጠፍተን ነበርን ተማርኬ በፍቅር አመልክሀለሁ ወድቄ ፊትህ በፈቃዴ ደስ እያለኝ ጌታ ኢየሱስ እወድሀለሁኝ እኔም ዋና ምስክር ነኝ አውቃለሁ ከየት እንዳነሳኸኝ በፍቅር እጆችህ እጆቼን እየያዝክ ከስንቱ ጥፋት መለስከኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection