ይሄ ቢሆንልኝ ብዪ የምመኘው ህልሜ እውን ሆኖ መች ነው የማየው ብዪ የማስበው የማልመው ነገር ተሰጥቶኛል አንተን ያገኘሁኝ ቀን ተራራ አልወጣሁ ወይ አልወረድኩኝ ግን እንዲሁ በፀጋህ ስለወደድከኝ ከምገምተው እና ከማስበው በላይ ቤት ሰርተህልኛል በሰማይ *2 አንተ ክብሬ ነህ አንተ ጥበቤ ቅድስናዪ የሱስ ቤዛዪ ምን አለኝ የምሻው ከእንግዲህ ሁሉም ተሰጥቶኛል በስምህ ፍቅርህን እያሰብኩ ሁሌ አመልክሀለሁ የእግዚአብሔር ልጅ ወድሃለሁ። አሁን ያንተ የሆነው ሁሉ የኔ ነው ፍለጋ አልሄድም ማዶ ማዶ እያየሁ የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ ከአንተ የተነሳ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ ካንተ የተነሳ የንጉስ ልጅ ነኝ። አንተ ክብሬ ነህ አንተ ጥበቤ ቅድስናዪ የሱስ ቤዛዪ ምን አለኝ የምሻው ከእንግዲህ ሁሉም ተሰጥቶኛል በስምህ ፍቅርህን እያሰብኩ ሁሌ አመልክሀለሁ የእግዚአብሔር ልጅ ወድሃለሁ። ነጻ ወጥቻለሁ ከሀጥያት አበሳ ባርነቴ ቀርቷል ካንተ የተነሳ አንተ መሀል ገብተህ እኔን አስመለጥከኝ ውርደቴን ስድቤን ሞቴን ወሰድክልኝ *2 እህህህ,,, የሱስ ሙላቴ ቅድስናዪ የሱስ ትምክህቴ ምን አለኝ የምሻው ከእንግዲህ ሁሉም ተሰጥቶኛል በስምህ ፍቅርህን እያሰብኩ ሁሌ አመልክሀለሁ የእግዚአብሔር ልጅ ወድሃለሁ።