ምስጋና አያኖርህ የፍጥረታት ቅኔ ማንም ሳይፈጠር ኖረህ ነበር ያኔ ፍጡር ያምልክ እንጂ ለህይወቱ ብሎ የማንም ውዳሴ አያኖርህ ችሎ ባይወጣም እልልታ ከፍጥረታት አለም አንተን የሚያኖርህ አምልኮ እኮ አይደለም ፅኑ ምሰሶ ነህ የህይወት መገኛ ከቶ አይደለህም የአምልኮ ጥገኛ ባያንስህም አምልኮ ባያንስህም ክብር እኔ እንደዉ መስዋዕቴን ከመሰዋት አልቀር አምልኮዬ በፊትህ ሞገስ ካገኘልኝ አንተን ከማምለክ ውጭ ሌላ ምን ደስታ አለኝ ኧረ አንተ ክበርልኝ እግዚአብሔር ክበርልኝ ኧረ አንተ ክበርልኝ አሁንም ክበርልኝ ኧረ አንተ ንገስልኝ እግዚአብሔር ንገስልኝ ኧረ አንተ ንገስልኝ በህይወቴ ንገስልኝ መላእክት በፊትህ ቅዱስ ቅዱስ ብለዉ ለክብርህ ሲሰግዱ ክብራቸውን ጥለዉ ሰማይ ተናወጠ ስለሆነው ነገር ምድርን ስለሞላ ያንተ ድንቅ ክብር ባናመሰግንህ የእጆችን ስራ ሰማዩ ዝም ቢል ምድር ባታወራ ግርማህ አይቀንስም ምን ይቀርብሀል ማንንም ሳትፈጥር ብቻህን ከብረሀል ባያንስህም አምልኮ ባያንስህም ክብር እኔ እንደዉ መስዋዕቴን ከመሰዋት አልቀር አምልኮዬ በፊትህ ሞገስ ካገኘልኝ አንተን ከማምለክ ውጭ ሌላ ምን ደስታ አለኝ ኧረ አንተ ክበርልኝ እግዚአብሔር ክበርልኝ ኧረ አንተ ክበርልኝ ዘላለም ክበርልኝ ኧረ አንተ ንገስልኝ እግዚአብሔር ንገስልኝ ኧረ አንተ ንገስልኝ አንተው ከፍ በልልኝ ላንተ ሚመጥንህ አምልኮ ባይኖርም ግን አጣሁኝ ብዬ ትቼ ዝም አልልም ነፍሴን አፈሳለሁ ሆኜ በእግሮችህ ስር የመኖሬ አላማ ነዉ የአንተ ክብር ክብር ይሁንልህ ላንተ እግዚአብሔር ይገባሀልና በሰማይ በምድረ (x2)