አንተ የልቤ ረሀብ የነብሴ ጥማት ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት ከምትገኝበት በመቅደስህ ሆነህ ሁሌ አስብሀለው ደስ የሚያሰኘውን ፊትህን እሻለው እፈልግሀለዉ እንደምትናፍቅ ዋላ ወደ ውሀ አግኝታ እስክትረካ ከዛ በበረሀ ምንም አይታያት ማንም አያስቆማት እንዲሁ አምላኬ (ነው የነብሴ ጥማት) x2 አገኘሁህ እና ጥሜን አረካኸው ግን ደግሞ እርካታዬ አንተን ሚያስናፍቅ ነው አሁንም አሁንም ልቤ ይፈልግሀል በነገሮች መሀል ሀሳቤ ይወሰዳል ወዳንተ ይሄዳል አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት ከምትገኝበት ዋና የልቤ ትኩረት ያይኔ ደግሞ ፍዘት የጆሮዬ ጉጉት ድምፅህን ለመስማት በእጅክ ለመነካት ረሀቤ ክብርህ ነው ውበትህ ጥማቴ በሰማዩ ስርአት ተወስዷል መሻቴ የምድርን ግሳንግስ ትቼ ወደ ኋላ ወዳንተ ሮጣለው (ዘወትር እንድሞላ) x2 አንተ የልቤ ረሀብ የነብሴ ጥማት ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት ከምትገኝበት ዋና የልቤ ትኩረት የአይኔ ደሞ ፍዘት የጆሮዬ ጉጉት ድምፅህን ለመስማት በእጅክ ለመነካት በእየለቱ ሙላኝ ልቤንም ለውጠው በኢየሱስ የነበረውን ሀሳብ በእኔም ደግሞ ሙላዉ በትላንቱ ሙላት ትዝታ መኖር አልፈልግም ዛሬም ትሻሀለች ነብሴ እንዳዲስ ከቶ አልለምድህም ፈልግሀለው (x2) በሙሉ ልቤ አንተን እሻሀለው ፈልግሀለው (x2) በሙሉ ሀይሌ አንተን እሻሀለው ፈልግሀለው (x2) በሙሉ ልቤ አንተን እሻሀለው ፈልግሀለው (x2) በሙሉ ሀይሌ አንተን እሻሀለው