Song Lyrics

የኢየሱስ መንገድ

Dawit Getachew
Amnihalehu
በዚህች ምድር ስኖር ብርቱ ሰልፍ ቢኖርም ንፋስ ማዕበሉ ሊጥሉኝ ቢጥሩም እምነቴን ሊፈትን ዙሪያዩን ቢዞርም የጠራኝ ክርስቶስ ስለኔ አሸንፎአል ሁሉንም እሮጣለሁ ይሄን የጽድቅ ጎዳና እሮጣለሁ ይሄን የህይወት መንገድ ወስኛለው መስቀሉን እያየሁ ልሄድ ከኢየሱስ ሌላ ላልወድ ወደ ኋላም ከቶ ላልሄድ ግብ ግብ ከኔ ጋር ብዙ ቢያዝለኝም ነፍስን በሚያደክም ትግል ውስጥ ብኖርም ስጋዩን እየጎሸምኩ ወደ ፊት እሔዳለሁ የምኖርለትን አላማ እያየሁ እሮጣለሁ ይሄን የጽድቅ ጎዳና እሮጣለሁ ይሄን የህይወት መንገድ ወስኛለው መስቀሉን እያየሁ ልሄድ ከኢየሱስ ሌላ ላልወድ ወደ ኋላም ከቶ ላልሄድ በፀጋው ጉልበት እታመናለሁ ብወድቅም እንኳን ዳግም እቆማለሁ ግን እስከ ፍፃሜ መስቀሉን እያየሁ የኢየሱስን መንገድ እኖረዋለሁ ኢየሱስን ነው አይኔ የሚያየው ኢየሱስን ነው ተስፋ የማደርገው መስቀሉን ብቻ ነው ትኩር ብዩ የማየው እስከፍጻሜ ለክብር እሮጣለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection