Song Lyrics

ይወራ

Dagmawi Tilahun
Lela Lela Lela
ሲወራ ቢዋል ቢታደር አይገልፅም ያምላኬን ፍቅር ሲወራ ቢዋል ቢታደር አይበቃም ላየሁት ነገር ፍቅሩን ልከፍል በምን አቅሜ በልቤ ገብቶ በስጋ ደሜ ካይምሮ በላይ ሆኖብኝ ፍቅሩ አይሰለቸኝም መዋል ማደሩ በልቤ ዙፍኑን የሰራ አያልቅም ስለሱ ቢወራ ታሪኬን በመስቀል የሰራው አያልቅም ስለሱ ቢወራ ይወራ የእሱ ፍቅር ይወራ አንድም ሳይቀር ይወራ የእሱ ሰላም ይወራ አልቀነሰም ይወራ የእሱ ምሕረት ይወራ ነው በየእለት ይወራ የእሱ ቸርነት ይወራ ያለ መሰልቸት ስሙልኝ ስሙልኝ ስለዚህ ወዳጅ ማረከኝ በፍቅሩ አይደለም በግዳጅ እዩልኝ እዩልኝ ይህንን ትሁት ማይወደውን ወዶ ለፍቅር የሚሞት ይወራ የእሱ በጎነት ይወራ በደረስኩበት ይወራ የእሱ ቅንነት ይወራ ውሸት የለበት ይወራ ሰውን መውደዱ ይወራ ያመኑት ቢከዱ ይወራ በየሰበቡ ይወራ አዛኝ ነው ልቡ ይወራ ይወራ ይወራ እስትፍስ ባለው ይወራ ጌታ በረዳው ይወራ አንደበት ባለው ይወራ እሱ ባገዘው ሲወራ ቢዋል ቢታደር አይበቃም ላምላኬ ፍቅር ሲወራ ቢዋል ቢታደር አይበቃም ላየውት ነገር ፍቅሩን ልከፍል በምን አቅሜ በልቤ ገብቶ በስጋ ደሜ ካይምሮ በላይ ሆኖብኝ ፍቅሩ አይሰለቸኝም መዋል ማደሩ ስሙልኝ ስሙልኝ ስለዚህ ጌታ በወረት ተይዞ አይለይም ላፍታ እዩልኝ እዩልኝ ይሄንን ደግ ክፉ ላረገበት መልካም የሚያረግ ከውርደት ለክብር የጠራኝ ደንዳናውን ልቤን የገራ ይወራ የእሱ በጎነት ይወራ በደረስኩበት ይወራ የእሱ ቅንነት ይወራ ውሸት የለበት ይወራ ሰውን መውደዱ ይወራ የመኑት ቢከዱ ይወራ በየሰበቡ ይወራ አዛኝ ነው ልቡ ስሙልኝ ስሙልኝ ይሄንን ጌታ በወረት ተይዞ አይለይም ላፍታ እዩልኝ እዩልኝ ይሄንን ደግ ክፉ ላረገበት መልካም የሚያረግ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection