Song Lyrics

እኔስ አለኝ

Dagmawi Tilahun
Kalih Kalena Gibre
አንደበቴ አይፈታም ሥራ ለምሥጋና ስለ ተሰራ የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል አማረልኝ ዕልልታ ይዟል አዝ፦ እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (4x) ሁሉም ነገር አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው የሚታየው አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው የሚሰማው አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው ክብር ዝና አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው አሃ አሃ አንተን ፈልጌ አሃ አሃ ውስጤማ ናፍቆ አሃ አሃ ፍቅርህ ገባብኝ አሃ አሃ በልቤ ዘልቆ አሃ አሃ ይኸው ሽብሸባ አሃ አሃ ለስምህ ጉዳይ አሃ አሃ የእኔስ እልልታ አሃ አሃ ይሂድ ወደላይ አዝ፦ እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (4x) አንተ በሰራኸው አልወስድም ምሥጋና ልቤን ከፈትኩ እንጂ ምን አደረኩና አንተ በሰራኸው አልወስድም ምሥጋና እንኳን ተቀንሶ መቼ ይበቃና ይኸው (2x) ዕልልታው ይኸው (2x) ይኸው (2x) ሽብሸባው ይኸው (2x) ይኸው (2x) እልልታው ይኸው (2x) ይኸው (2x) አምልኮው ይኸው (2x) ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና ባለቤቱ የዕልልታ ይኸውልህ ይኸው ጌታ ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና ባለቤቱ የዕልልታ ይገባሀል የእኔ ጌታ መሻቴ የእኔማ ደስታ የአምልኮ ሽታ አላማ የመፈጠሬ ለዚህ ነው ላምልክ አብሬ ቅሬታ የለም ትካዜ ምስጋናን ባሰብኩኝ ጊዜ አዝ፦ እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (4x) አንደበቴ አይፈታም ሥራ ለምሥጋና ስለ ተሰራ የልቤ ሀሳብ የአፌ ቃል አማረልኝ ዕልልታ ይዟል አዝ፦ እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (4x) ሁሉም ነገር አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው ገንዘብ ንብረት አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው ስልጣን ሹመት አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው ዘውዱ ንግሱ አላፊ ነው አምልኮ ግን ዘላቂ ነው አዝ፦ እኔስ አለኝ ዕልልታ እኔስ አለኝ (4x) ባለቤቱ የዕልልታ ይኸውልህ ይኸው ጌታ ባለቤቱ የምሥጋና እግዚአብሔር እርሱ አለና ባለቤቱ የዕልልታ ይገባሀል የእኔ ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection