Song Lyrics

አባባ

Dagmawi Tilahun
Kalih Kalena Gibre
የሲዖል ጣር ሲይዘኝ የሞት ወጥመድ ሲከበኝ ስማኝ ስለው አባባ ጩኸቴ ጆሮው ገባ አባባ አባቴ ቀንዴ ነው ረድኤቴ አባባዬ አባባ ጩኸቴ ጆሮው ገባ አባባ እግዚአብሔር አለቴ አምባዬ (2x) ትምክህቴ ጦሬ ነው ጋሻዬ (2x) ሰማይ ዝቅ አለ አምላኬ ወረደ (2x) ከአፉ እሳት እየነደደ (2x) ቁጣው ወጣ ጌታዬ በራ በቀል የእርሱ የአምላኬ የእርሱ ሥራ ለሚጠላኝ ወደረኛ ወየውለት ጌታ መጣልኛ ለሚጠላኝ ወደረኛ ወየውለት ዘመን መጣልኛ በአንተ ቅጥሩን እዘላላሁ በጭፍራው ላይ እሮጣለሁ አጥፋ ብሎኝ አውጥቶአቸው ቀስተ ሰይፉን አሳያቸው በቀኝህ አስር ሺህ ወደቁ ሳይቀርቡ ሺዎችም አለቁ እንደጋሻ እውነቱ ከበበኝ ከፍላፃ አስጣለኝ ሰማይ ዝቅ አለ አምላኬ ወረደ (2x) ከአፉ እሳት እየነደደ (2x) ኃይልን ለበስኩ አስታጠቀኝ የጠላቴን ጀርባ ሰጠኝ እንደ ጭቃ ረገጥኳቸው እንደ ትቢያ ፈጨኋቸው መክበቡን ዙሪያዬን ከበቡኝ አታልፍም ስንዝርም ብለውኝ በስቃያቸው ላይ እየሳቅኩ በሥምህ አሸነፍኩ ቁጣው ወጣ ጌታዬ በራ በቀል የእርሱ የአምላኬ የእርሱ ሥራ ለሚጠላኝ ወደረኛ ወየውለት ጌታ መጣልኛ ለሚጠላኝ ወደረኛ ወየውለት ዘመን መጣልኛ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection