አምላኬ ፊትህን መቼ አየዋለሁ ውዴ ሆይ አንተስ ጋር መቼ እደርሳለሁ አዝ፦ አቤቱ ነፍሴ አንተን ናፈቀች (2x) እንደ ዋላ ውኃ እንደተጠማች (2x) ውኃም እንጨትም በሌለበት ነፍሴ ተጠማች የአምላኳን ፊት ሥጋዬም ናፍቃ በምድረበዳ ኃይልህን ክብርህን እንድታይ ወዳ አዝ፦ አቤቱ ነፍሴ አንተን ናፈቀች (2x) እንደ ዋላ ውኃ እንደተጠማች (2x) ወዳንተ ወዳንተ እገሰግሳለሁ (4x) በመኝታዬ አስብሀለሁ ማለዳ ቀትር አወራሀለሁ ነፍሴ ከኋላ ተከተለችህ ውዴ ወዳጄ ፍቅሬ አለችህ አምላክ ወዴት ነው ዘወትር ሲል እምባዬ በዝቶ ምግብ ሲሆነኝ ወደ ምሥጋና ማደሪየህ ልግባ ነፍሴ እንድትጠግብ አንተን አስባ አዝ፦ አቤቱ ነፍሴ አንተን ናፈቀች (2x) እንደ ዋላ ውኃ እንደተጠማች (2x)