አምላኬ ሆይ ቃሌን ስማ ፀሎቴን አድምጥ ልመናዬ ይድረስልኝ አንዴ አስበኝ ናልኝ አስበኝ በአንተ ብቻ ተስፋ አለኝ አንዴ (2x) አስበኝ ሌላ ጥያቄ መሻት የለኝ ፀጋህ ሳያንሰኝ ምህረትሀ ሳይጎድል ምነው መዛሌ ምነው መታለል መንገድህ ባይሆን እንደመንገዴ እድልን ስጠኝ አስበኝ አንዴ አዝ፦ አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (2x) አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (2x) አትሰብር ከቶ ቅጥቅጥ ሸምበቆ መንፈሱ ደቆ ሰው ካንተ ርቆ አታጠፋውም ሚጤሰውን ጧፍ ግን ሳታስበኝ ጊዜው እንዳያልፍ አዝ፦ አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (2x) አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (2x) አሀአሀሀሀ አስበኝ አሀአሀሀ አስበኝ አስበኝ ጌታ አሀሀሀሀ ከአለት ንቃቃት ተሸሽጌያለሁ ክረምቱ ሲያልፍ ያኔ ወጣለሁ ለምትል ነፍሴ ለተጨነቀች የአንተን ጉብኝት አንዴ ትላለች አዝ፦ አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (2x) አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (2x) ያለቦታዬ ቦታን አግኝቼ በምድያም ሀገር ሰውን ፈርቼ ተነስ የሚል ድምፅ አንተ ፅኔ ሀያል ስታስብ እንጂ ከየት ይሰማል አዝ፦ አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (2x) አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (2x) አስበኝ እንደቃልህ አሀሀሀ የእኔ ጌታ እኔን አንዴ አስበኝ አትሰብር ከቶ አስበኝ መንፈሱ ደቆ እንደቃልህ አታጠፋውም አምላኬ ሆይ ግን ሳታስበኝ ጊዜው እንዳያልፍ አዝ፦ አስበኝ አስበኝ አንዴ አስበኝ (2x) አሳልፈህ ለፈቃዴ ከቶ አትስጠኝ (2x)