Song Lyrics

ይሰራል ጌታ

Dagmawi Tilahun
Kalih Kalena Gibre
አምላኬማ አምላክ ነውና ዛሬም ይኖራል ሳይለወጥ እየለወጠ ታሪክ ይሰራል አምላኬማ አምላክ ነውና ዛሬም ይኖራል ሳይቀየር እየቀየረ ታሪክ ይሰራል ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል ያለ ምሰሶ ሰማይ ቆሟል ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል ስንት ደካማ በዚያ ቆሟል አዝ፦ አቤት አቤት ሥራህ እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (2x) ስለ ጌታ የሚባል ብዙ ነገር ኖሮ እንዴት ልቤ ይግባ ሀዘን እንጉርጉሮ እንደሰው ልጅ ሀሳብ አይደለም መንገዱ ለበጎ ነው እንጀ እሱን ለወደዱ አዝ፦ አቤት አቤት ሥራህ እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (2x) ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል ያለ ምሰሶ ሰማይ ቆሟል ይሰራል ጌታ የአንተ እጅ አይቻለሁኝ ሁሉን ሲያበጅ ይሰራል ጌታ የአንተ ቃል ስንት ደካማ በዚያ ቆሟል በመጀመሪያ በፍጥረት ዓለም ግዑዝም ሕያው ከአንተ ጋር የለም ሁሉን ካመጣህ ከምንም ነገር ዛሬም ስለ እኔ ተናግረህ አይቀር አዝ፦ አቤት አቤት ሥራህ እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (2x) ይሰራል ጌታ የአንተ ሥም ወደ ላይ አይሄድም ደፍሮ ማንም ይሰራል ጌታ የአንተ መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ መርቶ ሚመልስ ይሰራል ጌታ የአንተ ሕግ ፍትህ ያለበት ፍርድ የሚያደርግ አዝ፦ አቤት አቤት ሥራህ እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (2x) የተዋበና የተራቀቀ የአምላኬ ሥራ እጅግ የላቀ መፈጠር እንጂ መፍጠር ማን ችሏል ማደስ ብቻ አይደል አዲስ ይሰራል አዝ፦ አቤት አቤት ሥራህ እኔስ ጌታ ወደድኩልህ/አየሁልህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection