Song Lyrics

ዕልልታ

Dagmawi Tilahun
Lela Lela Lela
ልቤም መልካም ነገር ይኅው አፈለቀ ውስጤን አረስርሶ በዛ አጥለቀለቀ መሬትን ፈንቅሎ ውኃ እንደሚወጣ ከልቤ የደስታ ጩኅት ዕልልታ ካፌ ወጣ ዕልልታ ዕልልታ ዕልልታ ዕልልታ /፫ ዕልልታ ነው ውስጤን የሞላው ዕልልታ ነው ባፌ ሚወጣው ዕልልታ ነው ውስጤን የሞላው ዕልልታ ነው ባፌ ሚወጣው ያ አስቸጋሪው ዝናብ ክረምቱ አለፈ ድምጼን ላሰማ ተነሳው የዜማ ጊዜ ደረሠ ከአለት ንቃቃትና ከገደል መሰሰጊያው ፡ ማልጄ ልነሣ ልውጣ ከበሮዬን ላንሣው ፡ ምድር ሁሉ እናመስግነው በመለከት እናመስግነው በበገና እናመስግነው በዕልልታ እናመስግነው ምድር ሁሉ እናመስግነው በመለከት እናመስግነው በበገና እናመስግነው በዕልልታ እናመስግነው ዕልልታ ዕልልታ ዕልልታ ዕልልታ /፫ ዕልልታ ነው ውስጤን የሞላው ዕልልታ ነው ባፌ ሚወጣው ዕልልታ ነው ውስጤን የሞላው ዕልልታ ነው ባፌ ሚወጣው በግብጽ ምድር ውስጥ በኩር ሲመታ በሞት አንዱ ሌላውን እንዳይረዳ እርሱም ጋር ደረሰበት ምድሪቱም ስትናወጥ በለቅሶ በዋይታ ፡ ደሙ ከለላዬ ሆኖ አሰማለሁኝ ዕልልታ ምድር ሁሉ እናመስግነው በክበሮ እናመስግነው በጸናጽል እናመስግነው በዕልልታ እናመስግነው ምድር ሁሉ እናመስግነው በክበሮ እናመስግነው በጸናጽል እናመስግነው በዕልልታ እናመስግነው ልቤም መልካም ነገር ይኅው አፈለቀ ውስጤን አረስርሶ በዛ አጥለቀለቀ መሬትን ፈንቅሎ ውኃ እንደሚወጣ ከልቤ የደስታ ጩኅት ዕልልታ ካፌ ወጣ ዕልልታ ዕልልታ ዕልልታ ዕልልታ /፫ ዕልልታ ነው ቤቴን የሞላው ዕልልታ ነው ሠፈሬ ሚሰማው ዕልልታ ነው ቤቴን የሞላው ዕልልታ ነው ሠፈሬ ሚሰማው ምድር ሁሉ እናመስግነው በክበሮ እናመስግነው በጸናጽል እናመስግነው በዕልልታ እናመስግነው ምድር ሁሉ እናመስግነው በክበሮ እናመስግነው በጸናጽል እናመስግነው በዕልልታ እናመስግነው ዕልልታ ነው ቤቴን የሞላው ዕልልታ ነው ሠፈሬ ሚሰማው ዕልልታ ነው ቤቴን የሞላው ዕልልታ ነው ሠፈሬ ሚሰማው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection