የኑሮ መክበዱን ሁሉ ነገር መወደዱ እህል ከጐተራ ሲጠፋ ፍሬም ባትሰጥ መሬት ታርሳ ቀና ብሎ ዓይን ሲያይ ደመና የለም በላይ ምድር ከሰማይ ይጠብቃል ሰማይ በምድር ላይ አፍጡዋል ጊዜው ቢወስድ ይህ ዝምታ አምላኬ ምድሬን እየረሳ ግን ጨለማው መበርታቱ ሊነጋ ነው ሌሊቱ ( 2x) አዝ፦ አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ የእግዚአብሔር ክንድ በምድሬ ሲነሳ የመከራው ዘመን ሲረሳ እምባ ካለቀሰው ሲታበስ የዘመናት/የአባቶቼ ጸሎት ሲመለስ ( 2x) አያለሁ አያለሁ አያለሁ አያለሁ አዝ፦ አያለሁ አያለሁ ገና ገና ገና ብዙ አያለሁ አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ የጦርነት ድምጽ ፈርቶ ካደገበት ቀይ ሸሽቶ በሰው ሃገር አንገት የደፋ የተናቀን የተገፋ ምድረ በዳውን ሲያቋርጠው በረሃው ሁሉም ሱያስጥለው ግን ሃገሩን ይዞ በልቡ ተበትኗል ሰሜን ደቡቡ ተስፋ ቢጨልም በሁሉ ነገር አንደበት ግን ክፉ አይናገር ያለፈው ይብቃ እርግማኑ የምትሰማ አያለሁ ( 2x) አዝ፦ አያለሁ አያለሁ ገና ገና ገና ብዙ አያለሁ አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ ሽባዎች አንካሶች ሲዘሉ ዲዳዎች ተናግረው ዕልል ሲሉ የታወረው ዓይን ሲበራ እግዚአብሔር/የማመልከው እራሱ ሲሰራ አያለሁ አያለሁ አያለሁ አያለሁ (፭x) ሃሌሉያ አያለሁ እኔ እኔ እኔ አያለሁ