Song Lyrics

ጌታን ነው የያዝኩት

Dagmawi Tilahun
Kalih Kalena Gibre
አንተ ባትደረስ ባታየኝ ኖሮ አይዞህ ያለኝ ሰው ድንገት ተሰብሮ ባበቃ ነበር እዛ ላይ እኔስ ታሪኬ አዋጅ ባይሻር የሞቴ ባንተ ባምላኬ (2x) ሰው አለኝ አይደለም ያልኩት ጌታን ነው እኔስ የያዝኩት (4x) መመኪያዬ መታመኛ ነው እሱን ይዤ ታዲያ እንዴት ፈራለሁ (2x) ሰው አለኝ አይደለም ያልኩት ጌታን ነው እኔስ የያዝኩት (2x) በስብርባሪውም እደርሳለሁ እንጂ አልቀርም ስምጬ ይዤ የአንተን እጅ ይዤ ጌታን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ሆ ይሞታል እያሉ ይጠባበቃሉ እሱን ይዞ ያፈረ ማንን ሰው ያውቃሉ ይዤ ጌታን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ሆ መመኪያዬ መታመኛ ነው እሱን ይዤ ታዲያ እንዴት ፈራለሁ (2x) በእርግጥ ወጀብ ካለ ታንኳ አይለቀቅም ና ካለኝ ግን ጌታ ልቀር አላስብም ይዤ ጌታን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ሆ በድካም በብርታት አሳልፎ የማይሰጥ እሱን መያዝ እንጂ ማዕበሉን ለማለፍ ይዤ ጌታን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ሆ ሰው አለኝ አይደለም ያልኩት ጌታን ነው እኔስ የያዝኩት (4x) ለዚህች አጭር ዘመን ለዚህች አጭር ጊዜ ቅርት ይበል ሁሉም ዘላለሜን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ሆ አንዱም አላረካኝ አንዱም ውስጤ አልገባ አንተን ስይዝህ ነው የደረቀው የኔ እንባ ይዤ ጌታን ይዤ ይዤ ጌታን ይዤ ሆ መመኪያዬ መታመኛ ነው እሱን ይዤ ታዲያ እንዴት ፈራለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection