Song Lyrics

ኢየሱሴ የምታልፈው

Dagmawi Tilahun
Kalih Kalena Gibre
አለም ሁሉ በእርሱ እያረፈ ይኼ ጌታ በዚህ እያለፈ ዝም አልልም እጮሀለሁ የዳዊት ልጅ እለዋለሁ (2x) እየሱሴ የምታልፈው የቆጠርከኝ እኔን ከሰው ባክህ ንካኝ አይኔን/ግባ ቤቴን ፈውሰው (2x) ዝም አልልም አታልፍም/ደርሶልኝ ቀኔ ዝም አልልም ሳይበራ/ልትበራ አይኔ ዝም አልልም አዳኜ መጥቶ አየዋለሁ አይኔ ተከፍቶ (2x) የሚጋፋ ግን የማይነካ የሚከፋው ለሰው ሲሳካ ተው ቢለኝም አልተውም እኔ ጨልሞብኝ አይለቅ ዘመኔ (2x) እየሱሴ የምታልፈው የቆጠርከኝ እኔን ከሰው ባክህ ንካኝ አይኔን/ግባ ቤቴን ፈውሰው (2x) ዝም አልልም አታልፍም/ደርሶልኝ ቀኔ ዝም አልልም ሳይበራ/ልትበራ አይኔ ዝም አልልም አዳኜ መጥቶ አየዋለሁ አይኔ ተከፍቶ (2x) እርሱ ጠርቶ ምን ይለመናል ብር ወርቅማ ሰውም ይሰጣል ልከተልሀ ፈውስ አይኔን መብራት የኔን ሰውነቴን (2x) በሰፈሬ በመንደሬ ሰምቻለሁ መልካም ወሬ መታሰሬ መታወሬ ታሪክ ይሁን ያብቃ ዛሬ አንዴ ልይህ አንተን ዛሬ (2x) እየሱሴ የምታልፈው የቆጠርከኝ እኔን ከሰው ባክህ ንካኝ አይኔን/ግባ ቤቴን ፈውሰው (2x) ዝም አልልም አታልፍም/ደርሶልኝ ቀኔ ዝም አልልም ሳይበራ/ልትበራ አይኔ ዝም አልልም አዳኜ መጥቶ አየዋለሁ አይኔ ተከፍቶ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection