Song Lyrics

ጌታ እርሱ ብቻ ነው

Dagmawi Tilahun
Geta Ersu Bicha New
በላይ በላይ በላይ በሰማይ በታች በታች ሆነህ በምድር ላይ (2x) አዝ፦ ጌታ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው አምላክ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው ዛሬስ የታሉ ታላቅ ነን ያሉ ዓመታት ሲያልፉ አብረው አለፉ የሁሉ ገዢ የሁሉ የበላይ የእኛ አምላክ ግን አለ በሰማይ (5x) አዝ፦ ጌታ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው አምላክ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው አላየሁኝም የሚመለክ እንደ እርሱ አላየሁኝም የሚወደድ እንደ እርሱ አልሰማሁኝም የሚመለክ እንደ እርሱ አልሰማሁኝም የሚወደድ እንደ እርሱ የምትወዱት ከእኔ ጋራ ተነሱ የሚገባውን ክብር እንስጥ ለእርሱ (2x) በላይ በላይ በላይ በሰማይ በታች በታች ሆነህ በምድር ላይ (2x) አዝ፦ ጌታ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው አምላክ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው የአህዛብ አማልክት የሚያመልኳቸው የማይሰሙና ማያዩ ናቸው ሰምቶ በእሳት የሚመልሰው የምናመልከው እግዚአብሔር ብቻ ነው (4x) አዝ፦ ጌታ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው አምላክ እርሱ ብቻ ነው (2x) ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው ያለውና የነበረው የሚመጣው ሁሌ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ ነው አልፋ እና ኦሜጋ እኔ ነኝ ብሏል ወዶ ፈቅዶ ፍጥረትም ያመልከዋል (2x) ጌታ እርሱ ብቻ አምላክ እርሱ ብቻ ገዢ እርሱ ብቻ ንጉሥ እርሱ ብቻ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection