የሰራኸውን ሳስተውለው ዞሬ አልጨርሰውም ሁሉንም ዘርዝሬ በፍቅር ቃላት እኔ ይህንን እላለሁ የወደደኝን እኔም እወደዋለሁ ጌታን እወደዋለሁ (4x) አዝ፦አንደበቴን ቀብቶታል ጌታ ኑሮዬን ባርኮታል (2x) ታዲያ ምኑ ዝም ያሰኘኝ ሁሌ ክብሩን እያሳየኝ (2x) ክበር ልበል ክበር እንጂ ንገሥ ልበል ንገሥ እንጂ ሌላ ቃላት ስለሌለኝ ሾሜሃለው ንገስልኝ ማነው የገመተ እዚህ ይደርሳል በሎ ጠላት ያለውን ወሬ ተቀብሎ ጌታ ሰው አረገኝ ጠላቴም አፈረ ማቄንም ቀደደ ቀንበሬን ሰበረ ጌታ ሰው አድርጐኛል (4x) አዝ፦አንደበቴን ቀብቶታል ጌታ ኑሮዬን ባርኮታል (2x) ታዲያ ምኑ ዝም ያሰኘኝ ሁሌ ክብሩን እያሳየኝ (2x) ክበር ልበል ክበር እንጂ ንገሥ ልበል ንገሥ እንጂ ሌላ ቃላት ስለሌለኝ ሾሜሃለው ንገስልኝ ባረከው ሕይወቴን ባረከው ኑሮዬን ስሾመው በላዬ ሳመልከው ጌታዬን በቀሪው ዘመኔም ጌታ ይንገስበት በሰጠኝም ሕይወት እርሱ ይሰልጥንበት ጌታን እሾመዋለሁ (2x) ጌታን አነግሰዋለሁ(2x) አዝ፦አንደበቴን ቀብቶታል ጌታ ኑሮዬን ባርኮታል (2x) ታዲያ ምኑ ዝም ያሰኘኝ ሁሌ ክብሩን እያሳየኝ (2x) ክበር ልበል ክበር እንጂ ንገሥ ልበል ንገሥ እንጂ ሌላ ቃላት ስለሌለኝ ሾሜሃለው ንገስልኝ (2x)