እንደኔ ማነው የእኔስ ልዩ ነው ወደቀ ሲባል ጌታ የሚያነሳው ኢየሱስ ረድቶኛል በሁሉ አብልጦ ከፍቶ አዲስ ምዕራፍ ታሪክ ለውጦ አዝ፦ ውለታው በዛ ጌታ ውለታው በዛ ውለታው በዛ ኢየሱስ ውለታው በዛ (2x) አቤት እንደኔ ማንን ረዳህ አቤት እንደኔ ማንን አገዝክ አቤት ምህረትህ የገነነለት አቤት እንደኔስ ማን በዛለት አዝ፦ ውለታው በዛ ጌታ ውለታው በዛ ውለታው በዛ ኢየሱስ ውለታው በዛ (2x) አስታውሳለሁ ከምን እንዳነሳኝ ሁሉም ሲጠየፍ እያየ ሲያልፈኝ ቁስሌን ጠራርጐ እምባዬን ሲያብስ አስቦ እኮ ነው እዚህ እንድደርስ አዝ፦ ውለታው በዛ ጌታ ውለታው በዛ ውለታው በዛ ኢየሱስ ውለታው በዛ (2x) አቤት እንደኔ ማንን ረዳህ አቤት እንደኔ ማንን አገዝክ (አቤት አቤት አቤት) አቤት ምህረትህ የገነነለት አቤት እንደኔስ ማን በዛለት አዝ፦ ውለታው በዛ ጌታ ውለታው በዛ (ውለታው) ውለታው በዛ ኢየሱስ ውለታው በዛ (2x) ክብሬ ትዘምር ዝምም አትበል ለቅሶዬን ለደስታ ጌታ ለውጧል ማቄንም ቀዶ ደስታ አስታጠቀኝ ምህረቱ በዝቶ በፊቱ አቆመኝ ምህረቱ በዛ ጌታ ምህረቱ በዛ ምህረቱ በዛ ኢየሱስ ምህረቱ በዛ ጥበቃው በዛ ጌታ ጥበቃው በዛ ጥበቃው በዛ ጌታ ጥበቃው በዛ ሰላሙ በዛ ጌታ ሰላሙ በዛ ሰላሙ በዛ ኢየሱስ ሰላሙ በዛ