Song Lyrics

ጠላት ተመቷል

Dagmawi Tilahun
Geta Ersu Bicha New
አዝ፦ እባብና ጊንጡን አስረግጦናል በጠላት ኃይልም ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል የሰላም አምላክ እግራችን ሥር ቀጥቅጦታል የሚያስቆመንም የለም ጠላት ተመቷል (2x) የጌታን ዕቃ ጦር እንለብሳለን አይደል በደም ሥጋ መጋደላችን የዲያቢሎስን ሽንገላ ተቃውመን በአለቆች ስልጣናት ላይ እንዘምታለን የሚመለመለውን የክፉ ፍላፃ እናጠፋዋለን አለን የእምነት ጋሻ አዝ፦ እባብና ጊንጡን አስረግጦናል በጠላት ኃይልም ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል የሰላም አምላክ እግራችን ሥር ቀጥቅጦታል የሚያስቆመንም የለም ጠላት ተመቷል (2x) እርሱ ከኛ ጋር ነው ማን ይቃወመናል በሕይወት ጐዳና ይኸው አራምዶናል እጃችንን ይዞ መቼ ማድረስ ብቻ በድል አሻግሮናል የሞትን ዳርቻ እርሱ ኃይላችን ነው መመኪያ ክብራችን መቼም አንወድቅ አለ ከጐናችን አዝ፦ እባብና ጊንጡን አስረግጦናል በጠላት ኃይልም ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል የሰላም አምላክ እግራችን ሥር ቀጥቅጦታል የሚያስቆመንም የለም ጠላት ተመቷል (2x) በኃይል አይደለም በብርታት የጠላት እንዲህ መመታት በመንፈሱ እንጂ በእግዚአብሔር ክንዱን ተማምኖ በሚኖር (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection