Song Lyrics

በችኮላ ከቶ አልወጣም

Dagmawi Tilahun
Geta Ersu Bicha New
በማስተዋል አደርጋለሁ እረኛዬን እሰማዋለሁ ያውቃል ከእኔ በብዙ ሺህ ነፍሴ ይምራሽ አምላክሺ ቀድሞ አይቶ የእኔን መንገድ መራኝ በድንቅ በእርሱ ፈቃድ ግራ ቀኜን ስላየልኝ ተማምኜ እወጣለሁኝ አዝ፦ በችኮላ ከቶ አልወጣም በመኮብለል ደግሞ አልሄድም እግዚአብሔር ይቀድመኛል በፈቃዱ ይመራኛል (2x) በድንኳኔ እጠብቃለሁ የአንተን ትእዛዝ እሰማለሁ ውጣ ካልከኝ እወጣለሁ ጠላቶቼን እመታለሁ ጠላት ለእኔ ለሚያስበው ግድም አይለኝ ስለሚለው የእግዚአብሔር ኃይል ሸፍኖኛል ደሙ እርሱ እኔን ስቦኛል አዝ፦ በችኮላ ከቶ አልወጣም በመኮብለል ደግሞ አልሄድም እግዚአብሔር ይቀድመኛል በፈቃዱ ይመራኛል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection