Song Lyrics

ለእኔ ምታስበው

Dagmawi Tilahun
Geta Ersu Bicha New
አዝ፦ ለእኔ የምታስበው ይበልጣል ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል እኔ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ መታመኔን በአንተ አደርገዋለሁ ጌታን እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ (2x) የሳቁ ነበሩ በአንተ ስታመን ትፈታዋለህ ስል እንቆቅልሼን ጠላቴም ወዳጄም ስታስበኝ አዩ የሚያመልከው አምላክ ለካ ይሰማል አሉ (2x) አዝ፦ ለእኔ የምታስበው ይበልጣል ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል እኔ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ መታመኔን በአንተ አደርገዋለሁ ጌታን እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ (2x) ቃልህን አምናለሁ አይደለም ስሜቴን እንደምትሞላው መሻቴን የውስጤን ፍፃሜና ተስፋ የምትሰጠዉ ሃሳብህ ይበልጣል እጠብቃለሁ (2x) አዝ፦ ለእኔ የምታስበው ይበልጣል ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል እኔ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ መታመኔን በአንተ አደርገዋለሁ ጌታን እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ (2x) በአንተ እታመናለሁ አልነዋወጥም ወደ ግራና ቀኝ አማራጭ አላይም ግድ ይልሃልና ጌታ የእኔ ነገር ከአንተ እጠብቃለሁ ወደሌላው ሳልዞር (2x) አንተን ብቻ እጠብቃለሁ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ የሕይወት ቃል አለህና ለዘላለም የሚያጸና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection