አዝ፦ የልቤ ደረሰ ያሰብኩት ተሳካ አደራ የሰጠሁት ኢየሱስ ነው ለካ (2x) ዛሬማ አርፌ ተደላድያለሁ ሥራዬ ተሰርቶ አመሰግናለሁ (2x) በሬን ዘግቼ የለመንኩት ምነው ባረገው ጌታን ያልኩት በእጥፍ ላከው ቀዶ ከሰማይ የልቤ ደርሷል ካሰብኩት በላይ (2x) አዝ፦ የልቤ ደረሰ ያሰብኩት ተሳካ አደራ የሰጠሁት ኢየሱስ ነው ለካ (2x) ዛሬማ አርፌ ተደላድያለሁ ሥራዬ ተሰርቶ አመሰግናለሁ (2x) የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ መች እዘነጋለሁ እዘምረዋለሁ የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ መች እዘነጋለሁ አመሰግናለሁ (2x) አዝ፦ የልቤ ደረሰ ያሰብኩት ተሳካ አደራ የሰጠሁት ኢየሱስ ነው ለካ (2x) ዛሬማ አርፌ ተደላድያለሁ ሥራዬ ተሰርቶ አመሰግናለሁ (2x) (የልቤ ደረሰ) (3x) አላየሁኝም ፃድቅ ሲጣል ዘሩም ሲለምን አጥቶ እህል ጌታ ታሪኬን እንዲህ አርጐታል የልቤን ሃሳብ አሳክቶታል (2x) የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ መች እዘነጋለሁ እዘምረዋለሁ የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ መች እዘነጋለሁ አመሰግናለሁ (2x)