የፍቅርህ ልክ የፍቅርህ ገደብ በዝቶብኝ እኔስ ለማሰብ አይጠፋም ሥምህ ከአፌ አይወጣም ፍቅርህ ከልቤ (2x) ቀስቃሽ አልፈልግም ሳመልክህ መች በረደ ውስጤ ያ ፍቅርህ ሲነድ ይሰማኛል በላዬ እወድሃለሁኝ ጌታዬ (2x) ኢየሱሴ ለኔ ምትክ የለህ ልቤም ሌላ አይሻ አንተ እያለህ ከፍ የምታደርግ በአንተ ጊዜ ዙፋንህ ሥር ልስገድ ሁልጊዜ ተባረካ ጌታዬ ተባርክ ተባረካ አምላኬ ተባረክ (2x) ምን ይከፈልሃል ጌታዬ (አሃሃ) ጌታዬ ሁሉ የአንተ ነው አምላኬ (አሃሃ) አምላኬ ምሥጋናና አምልኮ አምልኮ (አሃሃ) ምሥጋና መቼ ይበዛብሃል ትልቅ ነህ (አሃሃ) ገናና ተመስገንልኝ ጌታዬ ተመስገንልኝ ከሕያዋን ጋር ሥምህን አከብራለሁኝ ተባረክልኝ ጌታዬ ተባረክልኝ ከሚወዱህ ጋር ሥምህን አከብራለሁኝ እንዳለፈ ውሃ መከራዬን ረስቼዋለሁ ሳየው ጌታን እኔስ አልሰጋም ከእንግዲህስ ብዬ እዚህ ያደረስኝ አለ ጌታዬ አለ ጌታዬ (አለ) (8x)