አምኜው አልከዳኝም በእኔ ላይ አልፈረደም (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር የእኔ ዳኛ ትክክል እውነተኛ (2x) ሰው ፊትን አይቶ ሲፈርድ ጌታ ግን የልብን ነው ሁሉንም እንደስራው አይቶ ነው የሚከፍለው በፍርዱ አይጸጸት ለካ እንዲህ ነበር አይል አስተዋይ ጥበበኛ እርሱ ነው የኔ ዳኛ አዝ፦ እግዚአብሔር የእኔ ዳኛ ትክክል እውነተኛ (2x) እግዚአብሔር ክንደ ብርቱ ተቀምጦ በችሎቱ አይፈራ አያዳላ አይዋሽም እንደሌላ አፉ በፍርድ አይስት ሚዛኑ ትክክል ነው በእኔ ላይ ሳይሆን ለእኔ ፈረደልኝ መድህኔ ዳኛዬ እሱ ነው የእኔ ዳኛ (4x) በግራና በቀኙ አማካሪ አይፈልግም ቃሉንም የሚያርመው ከቶ አንድም አይገኝም እግዚአብሔር አዋቂ ነው ሥራውን ይመዝናል ውሳኔው መጨረሻው የእኔን ልብ አሳርፏል አዝ፦ እግዚአብሔር የእኔ ዳኛ ትክክል እውነተኛ (2x)