ተስፋ ርቆ ሲዞር የሚደግፍ ጠፍቶ ዘንበል የሚል ማነው እንደጌታ ራርቶ ጊዜ ወቅቱን አይተው ሰዎች ሲቀየሩ ጌታ ግን ታማኝ ነው ወረት የለው ፍቅሩ (2x) መሽቶ እስኪነጋ እስኪነጋ እስኪነጋ ያለውን ሊፈጽም የሚተጋ የሚተጋ አላየሁኝም በቃሉ የሚገኝ የሚገኝ አምላኬ ብቻ ብቻውን ታማኝ (2x) ታማኝ ነዉ ታማኝ ጌታ ታማኝ ነዉ ታማኝ (2x) ጌታዬ በአንተ ምኞቴ የልቤ ደረሰ አንተን መታመኔ እኔ መች ከንቱ ነበረ (2x) እሰዪ የልቤ ደረሰ ምርኮዬ በእርሱ ተመለሰ ተሞላ ልቤ በደስታ ልዘርም ታማኝ ነው ጌታ (2x) ታማኝ ነዉ ታማኝ ጌታ ታማኝ ነዉ ታማኝ (2x) እንግዲህ ምን ልበል ጨለማዬ በራ ከሸለቆ ወጣሁ ቆምኩኝ በተራራ (2x) ጌታዬ ባንተ ምኞቴ ያሰብኩት ተሳካ አንተን መታመኔ እኔ ልክ ነበር ለካ (2x) ልክ ነው ጌታዬ ልክ ነው እንዳለው ነው ለኔ ያደረገው ሁኔታ ቃሉን አለወጠው በእውነትም ጌታዬ ታማኝ ነው (2x) መሽቶ እስኪነጋ እስኪነጋ እስኪነጋ ያለውን ሊፈጽም የሚተጋ የሚተጋ አላየሁኝም በቃሉ የሚገኝ የሚገኝ አምላኬ ብቻ ብቻውን ታማኝ ታማኝ ነዉ ታማኝ ጌታ ታማኝ ነዉ ታማኝ (2x) በሀሩሩ ጥላ ብርሃን በጨለማ ምስኪን የምታግዝ ፀሎት የምትሰማ በሀሩሩ ጥላ ብርሃን በጨለማ እኔን የምታግዝ ፀሎት የምትሰማ