አንተው ነህ የእኔ መታመኛ አንተው ነህ የእኔ መደገፊያ (2x) እግዚአብሔር ትክክል ነው ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ማን ይቀራል እንባው ፈስሶ ይታበሳል ቀኑ ደርሶ መታመኛው እግዚአብሔር ማረፊያውም ከጥላው ሥር በኩፉ ቀናት ከጐኑ ሆኖለታል በዘመኑ አዝ፦ አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (2x) ጌታዬ መተማመኛዬ (4x) እንዳተ ያለ መልካም ለሰው የሚራራ የተዋረደውን ደርሶ የሚያኮራ አላገኘሁም እኔስ እስከ እድሜዬ ልክ እወድሃለሁኝ አንተ ነህ የኔ አምላክ አዝ፦ አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (2x) ጌታዬ መተማመኛዬ (4x) ቅዱስ ሥሙ እንዲጠራ ትልቅ ታሪክ በእኔ ሰራ ጠላቶቼን አሳፍሮ ታየ ጌታ በኔ ከብሮ አልቀረሁም እንደወደቅኩ ጌታን ይዤ መቼ አፈርኩ አጥር ቅጥሩን እየዘለልኩ እኖራለሁ እያመለኩ አዝ፦ አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (2x) ጌታዬ መተማመኛዬ (4x) አቅም ጉልበት ስለሌለው የት ይደርሳል የተባለው ዛሬ ታዲያ ለዚህ ክብር ለዚህ ሹመት ማን አበቃው ጌታ እኮ ነው የእርሱ ተስፋ መድረሻ አለው እንዳይጠፋ ያግዘዋል የታመነው ያኮራዋል የሚያመልከው አዝ፦ አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (2x) ጌታዬ መተማመኛዬ (4x) ቅዱስ ሥሙ እንዲጠራ ትልቅ ታሪክ በእኔ ሰራ ጠላቶቼን አሳፍሮ ታየ ጌታ በእኔ ከብሮ አልቀረሁም እንደወደቅኩ ጌታን ይዤ መቼ አፈርኩ አጥር ቅጥሩን እየዘለልኩ እኖራለሁ እያመለኩ አዝ፦ አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (2x) ጌታዬ መተማመኛዬ (4x) እንዳንተ ያለ መልካም ለሰው የሚራራ የተዋረደውን ደርሶ የሚያኮራ አላገኘሁም እኔስ እስከ እድሜዬ ልክ እወድሃለሁኝ አንተ ነህ የእኔ አምላክ አዝ፦ አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (2x) ጌታዬ መተማመኛዬ (4x)