እኔስ በአምላኬ በጌቶች ጌታ ይህ ነው አይባልም ያለኝ ደስታ ደመና ሳይኖር በአካባቢዬ ግራ ተጋብቷል ጠላት በደስታዬ (3x) አዝ፦ የደስታ መንፈስ በላዬ ወርዶ ሃዘን ምሬቴን ከውስጤ ወስዶ አመልከዋለሁ ከጠዋት ማታ ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ደስታ (ጌታ) (4x) የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ ሆኖ ሃዘኔ ጠፋ እንደጉም በንኖ አላማርርም አላንጐራጉር ደስተኛ ነኝ ሁሌ በእግዚአብሔር (3x) አዝ፦ የደስታ መንፈስ በላዬ ወርዶ ሃዘን ምሬቴን ከውስጤ ወስዶ አመልከዋለሁ ከጠዋት ማታ ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ደስታ (ጌታ) (4x) ማን ደስ ሊለው እኔ ልከፋ በትንሽ ትልቁ ደስታዬ አይጠፋ ለጠላት ወሬ ጆሮም አልሰጠው ደስታዬ ፍጹም መቼም ማይወሰድ ነው (3x) አዝ፦ የደስታ መንፈስ በላዬ ወርዶ ሃዘን ምሬቴን ከውስጤ ወስዶ አመልከዋለሁ ከጠዋት ማታ ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ደስታ (ጌታ) (4x)