Song Lyrics

ጌታ አለ ከጐኔ

Dagmawi Tilahun
Geta Ale Kegone
ሲሰማ ፉከራው ሽለላው የጠላቴ ወሬ (አሃሃ) የጠላቴ ወሬ (2x) ሰው የሚተርፍ አይመስልም እኔ ግን አለሁ እስከዛሬ (አሃሃ) አለሁ እስከ ዛሬ (2x) ተዉኝ ሌላ አልሰማም ቢፎክር ሁሉም ለጊዜው ነው (አሃሃ) ሁሉም ለጊዜው ነው (2x) የሚያስፈራም ሆነ የሚያስደነግጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው (አሃሃ) እግዚአብሔር ብቻ ነው (2x) ያረገውን አስቤ ከልቤ ኦ ከልቤ ማደሪያው ዙፋኑን ከብቤ ኦ ከብቤ ምሥጋና አምልኮ እላለሁ እኔማ መች ጠገብኩ ረካሁ (2x) አለኝ ብዙ ሥራ ልነሳ ተረኛ ነኝ እኔ (አሃሃ) ተረኛ ነኝ እኔ (2x) አትበሉ የልጅ ነገር እዩ እንጂ ጌታ አለ ከጐኔ (አሃሃ) ጌታ አለ ከጐኔ (2x) የሚመችም ባይሆን ቢከፋ ቢበዛም ውጊያዉ (አሃሃ)ቢበዛም ውጊያዉ (2x) እኔ አልመለስም ፈርቼ ጌታን ይዣለሁ (አሃሃ) ጌታን ይዣለሁ (2x) ያረገውን አስቤ ከልቤ ኦ ከልቤ ማደሪያው ዙፋኑን ከብቤ ኦ ከብቤ ምሥጋና አምልኮ እላለሁ እኔማ መች ጠገብኩ ረካሁ ምሥጋና አምልኮ እላለሁ ለኔማ ብዙ ነው የሆንከው የክብሩ ደመና መንፈሱ በላዬ አለፈ (አሃሃ)በላዬ አለፈ (2x) ጓዙን ጠቀለለ ሀዘኔ በአንተ ተገፈፈ (አሃሃ) ባንተ ተገፈፈ (2x) የሰማዩ አዋጅ ዜናው ለእኔ ምስራች ነው (አሃሃ) ለኔ ምስራች ነው (2x) ምንም ነገር ባይኖር አምላኬ ከበቂ በላይ ነው (አሃሃ) ከበቂ በላይ ነው (2x) ያረገውን አስቤ ከልቤ ኦ ከልቤ ማደሪያውን ዙፋኑን ከብቤ ኦ ከብቤ ምሥጋና አምልኮ እላለሁ እኔማ መች ጠገብኩ ረካሁ (2x) ምሥጋና አምልኮ እላለሁ ለእኔማ ብዙ ነው የሆንከው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection