አምላኬ እድሌ ፈንታዬ ያለመለምከው ተስፋዬን መሞት ሲገባኝ ኩነኔ እኔስ ገረመኝ መዳኔ (2x) ገረመኝ መዳኔ መዳኔ ገረመኝ መዳኔ (2x) ውለታ ያለበት መች ውስጡ ዝም ይላል እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል ፍቅሩን የቀመሰ መች ውስጡ ዝም ይላል እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል ያደረግልኝን ጌታ ይሆነልኝን አስቤው ያን ዘመን በርሱ ያለፍኩትን ክበር ልበለው እየደጋገምኩኝ ንገሥ ልበለው እየደጋተምኩኝ ክበር ልበለው አከብረዋለሁኝ ንገሥ ልበለው አነግሰዋለሁኝ ቅጥቅጥ ሸንበቆ አትሰርም የወደቀ አይተህ አታልፍም አልቀረሁ ምስኪን ተብዬ ባንተ ሰው ሆንኩኝ ጌታዬ (2x) ሰው ሆንኩኝ ጌታዬ (3x) ቃሉን ያሰበ መች ውስጡ ዝም ይላል እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል ከሞት ያመለጠ መች ውስጡ ዝም ይላል እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል ያደረግልኝን ጌታ ይሆነልኝን አስቤው ያን ዘመን በርሱ ያለፍኩትን ክበር ልበለው እየደጋገምኩኝ ንገሥ ልበለው እየደጋተምኩኝ ክበር ልበለው አከብረዋለሁኝ ንገሥ ልበለው አነግሰዋለሁኝ ቤቴ በክብሩ ተሞላና እኔም ወግ አየሁ እንደገና (2x) ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ ሳልሰለች በደስታ ልዘምር ለጌታ ከሆንኩለት በላይ ምነው በሆንኩለት (3x) ሕይወቴ ያማረው እርሱን ያገኘሁ እለት (3x) አንደበቴን ልክፈት በብዙ ምሥጋና (3x) በቅቶኝ አልቀመጥ ውስጤ ይላል ገና (3x) ውስጤ ይላል ገና ውስጤ ይላል ገና ይላል ገና ውስጤ ይላል ገና (2x) ይላል ገና ምሥጋና ይላል ገና ገናና ይላል ገና አምልኮ ይላል ገና ዝማሬ (4x)