መልካም ዘመን ወይም ክፉ አያወጡኝ ከእቅፉ ዓይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው አለው ለእኔ ያዘጋጀው አጋጣሚውን ልቤ አይቶ አይሸፍትም ከሱ ወጥቶ ግራ ገብቶኝ ዝዬ አልቅሼ ጌታ አይደል ዎይ አስታዋሼ አዝ፦ አይረሳም ሰው አይረሳም (4x) እስኪ ልናገር ካልኩት በላይ ነው የእርሱ ነገር በዓለም ያልታየ በሰው የሌለ የሰማይ ፍቅር እስኪ ልናገር ካልኩት በላይ ነው የእርሱ ስራ በዓለም ያልታየ በሰው የሌለ አያልቅ ቢወራ እጄን ይዞ እንዳልዎድቅ ሲራራልኝ ሲጠነቅቅ አቤት ሲያዝን አቤት ሲሳሳ የኔን ነገር ፍፁም አይረሳ (2x) አዝ፦ አይረሳም ሰው አይረሳም (4x) ስላለፈው ስጨነቅ ስለነገው ስታወክ መለስ ስል ወደ ልቤ ጌታ እኮ አለ አጠገቤ ምክንያቱ ነው ለመኖሬ ለሱኮ ነው መፈጠሬ ከበደኝ አይል ሲሸከመኝ ከኔ ጋር ነው መቼ ረሳኝ እስኪ ልናገር ካልኩት በላይ ነው የእርሱ ነገር በዓለም ያልታየ በሰው የሌለ የሰማይ ፍቅር እስኪ ልናገር ካልኩት በላይ ነው የእርሱ ስራ በዓለም ያልታየ በሰው የሌለ አያልቅ ቢወራ እጄን ይዞ እንዳልዎድቅ ሲራራልኝ ሲጠነቅቅ አቤት ሲያዝን አቤት ሲሳሳ የእኔን ነገር ፍፁም አይረሳ (2x) አዝ፦ አይረሳም ሰው አይረሳም (4x) እናት ልጇን ብትረሳ ዓይኗን ከእርሱ ብታነሳ ብትሸከም አልፈጠረች እንደሌላው ሰው እኮ ነች በእስትንፋሱ የሰራኝ ግን ሊያጣኝ አይወድ ሌትና ቀን ዋጋ ከፍሎ ዋጋ ሰጠኝ መች ሊረሳ መች ሊተወኝ ለካ ሸክሙ የሚከብደው ሰው ለብቻው ሲዪዘው ነው ሲደርስልኝ በድካሜ እርፍ አልኩኝ ከህመሜ ቀን ያነሳው ቀን ቢሽረው ጌታ ያሰበውን ሰው አይጥለው በንስር ክንፍ በከፍታ ያወጣኛል የእኔ ጌታ አዝ፦ አይረሳም ሰው አይረሳም (4x)