ዓመቱ የታለ ወራትና ቀኑ እርግጥ አይኖርም ክፉ ነው ዘመኑ አንተማ ዛሬም ያው ትላንት እንደ አዩህ ስትለውጥ እንጂ ተለውጠህ አያውቁህ (4x) አዝ፦ (አንተማ አንተማ) አትለዋወጥም (አንተማ) አትቀያየርም (አንተማ) መቼ እንደሰዉ (አንተማ) ፍቅርህ ልዩ ነዉ (2x) ኢየሱሴ መድኃኒት ለነፍሴ ኢየሱሴ ማምለጫ ለነፍሴ (2x) ወዳጅ ወዳጅ ወዳጅ እንዳለው ሰዉ እኔም ካንተ ጋራ እወዳጃለሁ አምላክ አምላክ አምላክ እንዳለው ሰዉ እኔም ከአንተ ጋራ መኖር እሻለሁ አዝ፦ (አንተማ አንተማ) አትለዋወጥም (አንተማ) አትቀያየርም (አንተማ) መቼ እንደሰዉ (አንተማ) ፍቅርህ ልዩ ነዉ (2x) ኢየሱሴ መድኃኒት ለነፍሴ ኢየሱሴ ማምለጫ ለነፍሴ (2x) ብትወደኝ እኮ ነው ይኸው እስከዛሬ በፍቅርህ ታስሬ አብሬ መኖሬ አመል ሆኖብኛል አንተን አንተን ማለት ወዳጅ ስትሆነኝ ወረት የሌለበት (4x) አዝ፦ (አንተማ አንተማ) አትለዋወጥም (አንተማ) አትቀያየርም (አንተማ) መቼ እንደሰዉ (አንተማ) ፍቅርህ ልዩ ነዉ (2x) ኢየሱሴ ጠበቃ ለነፍሴ ኢየሱሴ ዋስትና ለነፍሴ ኢየሱሴ አለኝታ ለነፍሴ ኢየሱሴ መከታ ለነፍሴ (2x)