አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የሞትክልኝ በእኔ ቦታ አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የቆምክልኝ በእኔ ቦታ (ኧኸ) ጅማሬዬ ላይ (ኧኸ) ታሪክ ሲዘጉ (ኧኸ) ቁጣህ ነደደ (ኧኸ) አንተን እንደነኩ (ኧኸ) ወጪ ወራጁ (ኧኸ) የሚቀናበት (ኧኸ) ክብርህ ፈሰሰ (ኧኸ) ገባ ከእኔ ቤት አዝ፦ ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ) ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (2x) (ኧኸ) ሲማማምሉና (ኧኸ) ሲማከሩብኝ (ኧኸ) ፍላጻህ ወርዶ (ኧኸ) አፈረሰልኝ (ኧኸ) በጠላት ቀዬ (ኧኸ) በጠላት መንደር (ኧኸ) ስለአለኝታዬ (ኧኸ) እስኪ ልዘምር አዝ፦ ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ) ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (2x) ጠላቴ ብዙ ለፍቶ በእጁ ሊያስገባኝ ጓግቶ ፍቅርህ ያሰረው ልቤ አንተን አለኝ ሀሳቤ (2x) አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የሞትክልኝ በእኔ ቦታ አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የቆምክልኝ በእኔ ቦታ (ኧኸ) ማለዳ ቀትር (ኧኸ) ነግቶ እስኪመሽ (ኧኸ) በእኔ ዝማሬ (ኧኸ) ጠላት ሲረበሽ (ኧኸ) የማታው ለቅሶ (ኧኸ) ጠዋት ደስታ (ኧኸ) እንዲህ ነው እንጂ (ኧኸ) ማረፍ በጌታ አዝ፦ ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ) ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (2x) ጥቃቴን ከላይ አይተህ ክብርህን ለእኔ ትተህ ወርደህ ያወጣኸኝ ሞተህ ያተረፍከኝ (2x) አዝ፦ ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ) ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (3x)