Song Lyrics

ፍቅር ይቅር ያለው

Dagmawi Tilahun
Fikir Yikir Yalew
ኧረ እኔ ማነኝ ቤቴስ ምንድነው ከጣሪያዬ በታች ኢየሱስ የገባው (2x) ምህረት የበዛለት ፍቅር ይቅር ያለው ደግሞ ያየ ቸርነቱን እንደ እኔ ያለ ማነው (2x) (እኔማ) ሞተ ስባል ያለሁ (እኔማ) ጠፋ ስባል የቆምኩ (እኔማ) ምንም እንዳላየ (እኔማ) እንዴት ዝም እላለሁ (እኔማ) እኔማ ስላንተ (እኔማ) ለሃገርለምድሩ (እኔማ) አልጠግብ አውርቼ (እኔማ) ምህረት አግኝቼ ምህረት የበዛለት ፍቅር ይቅር ያለው ደግሞ ያየ ቸርነቱን እንደኔ ያለ ማነው (2x) በምህረትህ ብዛት ቤትህ እገባለሁ አንተ ራርተህልኝ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x) አቤቱ የወደቀውን እንዴት አየኸው አቤቱ የተረሳውን እንዴት አሰብከው ምህረትህ ምህረትህ እጅግ ብዙ ነው ፍቅርህ ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው (2x) አቤቱ ታናሹን ሰው እንዴት አየኸው አቤቱ የተጠላውን እንዴት ወደድከው ምህረትህ ምህረትህ እጅግ ብዙ ነው ፍቅርህ ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው (2x) (እኔማ) ያንን ዘመን ሳስብ (እኔማ) እንባ ይቀድመኛል (እኔማ) ሞት ሽረት ሆኖብኝ (እኔማ) ማን አለሁ ብሎኛል (እኔማ) ከበለሱም በታች (እኔማ) ድምጽህን መስማቴ (እኔማ) ያ ነው ሰው ያረገኝ (እኔማ) የመኖር ምክንያቴ ኧረ እኔ ማነኝ ቤቴስ ምንድነው ከጣሪያዬ በታች ኢየሱስ የገባው (2x) አቤቱ የወደቀውን እንዴት አየኸው አቤቱ የተረሳውን እንዴት አሰብከው ምህረትህ ምህረትህ እጅግ ብዙ ነው ፍቅርህ ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection