Song Lyrics

አየልኛ

Dagmawi Tilahun
Fikir Yikir Yalew
ያረገልኝ እንዴት ይረሳል አበቃ ስል ጌታ ጀምሯል (2x) ውለታው ብዙ ብዙ ፍቅሩ ብዙ ብዙ ሰላሙ ብዙ ብዙ ምህረቱ ብዙ ብዙ ጌታ አለብኝ ያንተ ውለታ (4x) መች እዘገናለሁ የትላንቱን አስታውሰዋለሁ እያንዳንዱን (2x) እኔ ነኝ የማውቀው እኔ ነኛ ከጐኔ ሰው ሳይኖር ወይ ጓደኛ እኔ ነኝ የማውቀው እኔ ነኛ የዛሬው ከፍታ ታየልኛ (2x) አዝ፦ አየልኛ ብዙ መልካም አየልኛ ለኔው ሰላም አየልኛ ብዙ እረፍት አየልኛ የማልፍበት (2x) ያረገልኝ እንዴት ይረሳል አበቃ ስል ጌታ ጀምሯል (2x) ውለታው ብዙ ብዙ ፍቅሩ ብዙ ብዙ ሰላሙ ብዙ ብዙ ምህረቱ ብዙ ብዙ ጌታ አለብኝ ያንተ ውለታ (4x) ያ ታሪኬ ዛሬ ተቀይሮ ሰው አይቶም አያውቀኝ አብሮኝ ኖሮ ያ ታሪኬ ዛሬ ተቀይሮ የቅርብ አይለየኝ አብሮኝ ኖሮ አትፈልጉ ሌላ እኔ ነኝ በምህረቱ ብቻ የቆምኩኝ አትፈልጉ ሌላ ራሴ ነኛ እንዲሁ በፀጋው ወደደኛ (2x) ወደደኛ ያኔ ድሮ ወደደኛ ሌላው ዞሮ ወደደኛ ሳይቀየር ወደደኛ በዛው ፍቅር (2x) ያረገልኝ እንዴት ይረሳል አበቃ ስል ጌታ ጀምሯል (2x) ውለታው ብዙ ብዙ ፍቅሩ ብዙ ብዙ ሰላሙ ብዙ ብዙ ምህረቱ ብዙ ብዙ ጌታ አለብኝ ያንተ ውለታ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection