Song Lyrics

ሳመልክህ እንድኖር

Dagmawi Tilahun
Fikir Yikir Yalew
ሳመልክህ እንድኖር ውስጤ ሳይል ዝም ምነው ቀኑ ባይኖር ሌቱም ባይጨልም መንፈሱን ፈልጌ ተዘልዬ እኔማ ሰከንዷም አትለፍ ድምጼ ሳይሰማ (2x) አዝ፦ እኔማ እንዴት ችዬ ዝም እኔማ አምልኮዬ አይቆም (2x) ጌታዬ መጣና እንባዬን አየና ነገሬን ፈወሰው የልቤ ደርሰ አይደለም ከሩቅ አለሁ ባዬ እንዲህ ነው ሲሰራ ጌታዬ (2x) እንዳሰብኩት ባይሆን (ይሁና አዋቂ ነውና) የልቤ ባይሞላ (ይሁና አዋቂ ነውና) መልሴ ቢዘገይም (ይሁና አዋቂ ነውና) ቅትር ላይ ቢጨልም (ይሁና አዋቂ ነውና) ምክንያቴን ጥዬ ሰበቤን ትቼ አመልካለሁኝ አምላክ አግኝቼ (2x) ሳመልክህ እንድኖር ውስጤ ሳይል ዝም ምነው ቀኑ ባይኖር ሌቱም ባይጨልም መንፈሱን ፈልጌ ተዘልዬ እኔማ ሰከንዷም አትለፍ ድምጼ ሳይሰማ (2x) አዝ፦ እኔማ እንዴት ችዬ ዝም እኔማ አምልኮዬ አይቆም (2x) እረስቶታል አሉ (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ) አባትነቱ የታል (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ) ህልሜን ህልም ቢሉት (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ) ሆኖ እስከሚያዩት (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ) ምክንያቴን ጥዬ ሰበቤን ትቼ አመልካለሁኝ አምላክ አግኝቼ (2x) ኢየሱሴ መጣና እንባዬን አየና ነገሬን ፈወሰው የልቤ ደርሰ አይደለም ከሩቅ አለሁ ባዬ እንዲህ ነው ሲሰራ ጌታዬ (2x) አዝ፦ እኔማ እንዴት ችዬ ዝም እኔማ አምልኮዬ አይቆም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection