አዝ:- ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (2x) መረጠኝ ሳልመርጠው ፈለገኝ ሳልፈልገው ከዜምናት በፊት ያሰበውን አደረገው ማን ሊከለክለው ነው ኧረ ማን ሊቃወመው ኃጢአተኛውን ወዶት በደሙ ከቀደሰው አዝ:- ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (2x) የሞት መውጊያው ተሰብሮ ስልጣን አጣ በእኔ ላይ አልቻለም ሊያስቀረኝ ከመንግሥተ ሰማይ አልመለስባትም ወደ እዚያች መራራ ዓለም ከእንግዲህ የኢየሱስ ነኝ እስከ ዘለዓለም አዝ:- ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (2x) ሳላውቀው ያሰረኝን የገዛኝን ረገጥኩት ክፉ ባለጋራዬን አለሁ እየተበቀልኩት ኃይል አለው መንፈስ አለኝ ባዶዬን አይደለሁም ደፍሬው እዋጋዋለሁኝ ጠላቴን አልሸሸውም አዝ:- ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (2x) ለክፋት የፈጠኑት እግሮቼ ዛሬ ሰክነው ማዳኑን ለመናገር ለወንጌል እየሮጡ ነው የታሰሩ እንዲፈቱ እንደ እኔ እንዲለቀቁ ከጨለማ ዓለም ወጥተው እንደ ፀሐይ እንዲደምቁ አዝ:- ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (2x)