Song Lyrics

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

Caleb Tesfaye
Motin Yereta Geta
አዝ፦ ባዶ ሸለቆን ይሞላል ምድረ በዳውን ያለመልማል ነፋስ ዝናብ ባይኖርም ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም (2x) ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) የቤት የጓዳው መብል ተሟጦባቸው ድረስ ና ላሉት በእንባ በጸሎታቸው እየጮሁ ለተማጸኑት መንገድ አለው መላ በመልሱ የሚያሳርፍበት የደረቀውን ኑሮ በቸርነቱ የሚያለመልምበት አዝ፦ ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) ባዶ ሸለቆን ይሞላል ምድረ በዳውን ያለመልማል ነፋስ ዝናብ ባይኖርም ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) የቀጠረለትን ቀን ምስኪኑን የሚባርክበት ይጠብቃል አውቀን ምን እንደተዘጋጀለት ያያል እጁ ሲገባ ሲያቆምለት ያን የደም እንባ የሱም ደሳሳ ጐጆ ሰው በማይንቅ አምላክ ታስባ አዝ፦ ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) ባዶ ሸለቆን ይሞላል ምድረ በዳውን ያለመልማል ነፋስ ዝናብ ባይኖርም ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) ድንጉጥ ልበ ፈሪዎች ለሰጉ ለተጠራጣሪዎች ስለ ነገ ተጨንቀው የትላንቱን ተዓምር ለረሱ ሰዎች መልዕክት አለው ዛሬም እኔ እኔ ነኝ አልተለወጥኩም ይመስክሩ ልጆቼ ተስፋ ያረጉኝን አላሳፈርኩም አዝ፦ ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) ባዶ ሸለቆን ይሞላል ምድረ በዳውን ያለመልማል ነፋስ ዝናብ ባይኖርም ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) ቀንበር ለከበዳቸው የዚህ ዓለም ኑሮ ለመረራቸው ቀኙን ግራውን ቢሉ ቢንከራተቱ ላልሞላላቸው እንጀራ ላጡ እንጀራ ባርኮ ሰጥቶ ያቀርባችኋል ብዙ ረሃባችሁን በብዙ ጥጋብ ይለውጥላችኋል አዝ፦ ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x) ባዶ ሸለቆን ይሞላል ምድረ በዳውን ያለመልማል ነፋስ ዝናብ ባይኖርም ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection