Song Lyrics

አምላኬ

Caleb Tesfaye
Motin Yereta Geta
አዝ፦ አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ አቤት ሲችል ሲያውቅበት አቤት ሲችል ሲያውቅበት አቤት ሲችል ሲያውቅበት (2x) ከቤት ከመንደሩ ከአባቱ ቤት ወጣ ዘሩን እንደ አሸዋ ሊያበዛለት መጣ የብዙ ህዝብ አባት በኩር አደረገው መሃኑን አብረሃም በልጅ ልጅ ባረከው (3x) አዝ፦ አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ አቤት ሲችል ሲያውቅበት (3x) የገዛ ወንድሞቹ ለባዕድ ሰዎች ሸጡት በህልሙ አንዳች እንዳይሆን አሳልፈው ሰጡት ነገ ነገን ወልዶ እውነቱ ወጣና ወድቀው ሰገዱለት ዮሴፍ ተሾመና (3x) አዝ፦ አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ አቤት ሲችል ሲያውቅበት (3x) የበግ ጅራት ሲከተል ግራገሩ እረኛ ንግሥናውን አያውቅ መሆኑን ተረኛ ውጣ ውረዱን አልፎ በትሩን በእጁ ሰጠው እልፍ ገዳይ አምላክ ዙፋን ላይ አስቀመጠው (3x) አዝ፦ አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ አቤት ሲችል ሲያውቅበት (3x) አናብስቶች ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት ቀንተውበት ከፀሎት ሌላ ምክኒያት ሰበብ አጥተውበት አልፈቀደላቸውም እንዲቀለጣጥሙት የዳንኤልን አምላክ ተባለ አምልኩት (3x) አዝ፦ አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ አቤት ሲችል ሲያውቅበት (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection